Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

በቤኒሻጉል ጉሙዝ መንግስት የላብራቶሪ ማዕከል በባለፉት 2013 ዓ.ም የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆኑ ተገለፀ

በቤኒሻጉል ጉሙዝ መንግስት የላብራቶሪ ማዕከል በባለፉት 2013 ዓ.ም የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆኑ ተገለፀ ። የክልሉ ላብራቶሪ ማዕከል የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የ2013 ዓ.ም የስራ አፈጻጸም ግምገማ አድርጓል ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ሪጅናል ላብራቶሪ ሀላፊ አቶ ገርብ ሎላሳ የግምገማ መድረኩን ሲከፊቱ እንዳሉት የክልሉ ላብራቶሪ ማዕከል በክልሉ ሥራ ከጀመረ አመታትን በማስቆጠር ላይ ቢሆንም በዚህ መልኩ የባለድርሻ አካላትን ባካተተ መልኩ የሥራ አፈፃፀም ስደረግ የመጀመሪያ መሆኑን ነው ። ይህ የግምገማ መድረክ የተመረጡ የጤና አጠባበቅ ጣቢያቸው እና የሪጅናል ላብራቶሪ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ዉይይት የሚደረግበትና በተቋማት መካከል የልምድ ልዉዉጥ የሚደረግበት መድረክ መሆኑን ገልጸዋል ። አቶ ገርብ አክለውም በማዕከሉ የተሟላ የሥራ ግብዓቶች የሰው ሀይልና እና በቂ በጀት ባልተሟሉበት የተሰሩ ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልፀው በተለይ በኮቭድ 19 መከላከል የተሰሩ ሥራዎች ምንጊዜም የማይረሱ ተግባራት ናቸው ብሎአል። የግምገማ መድረክ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የግምገማ መድረኩ መዘጋጀቱ በጣም ጥሩ መሆኑን ገልፀው እንዲህ አይነት መድረኮች መዘጋጀታቸውን ቅንጅታዊ አሠራሮችን ለማጠናከር የጎላ ድርሻ ስለአላቸው ተጠናክሮ መቀጠል አለባቸው ብለዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ