Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

ተነሳሽነት፤ብቁና ርህራሄ የተሞላበት የጤና ሰራተኞች በጤና ተቋማት መፍጠር ላይ ያተኮረ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ

(9/07/2014 ዓ.ም) በጤና ተቋማት ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰቡን የጤና ችግሮች ለማሻሻል ተነሳሽነት፤ብቁና ርህራሄ የተሞላበት የጤና ሰራተኞች በጤና ተቋማት መፍጠር ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ፡፡ የቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል መንግሰት ጤና ቢሮ ተነሳሽነት፤ብቁና ርህራሄ የተሞላበት የጤና ሰራተኞች በጤና ተቋማት ለመፍጠር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ለጤና ተቋም ሀላፊች እን ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅቷል ፡፡ የቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል መንግሰት ጤና ቢሮ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል የቢሮ ሀላፊ አቶ ወልተጅ በጋሎ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩን ሲከፊቱ እንዳሉት በጤና ተቋማት ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጥ የህብረተሰቡን የጤና ችግሮች ለማሻሻል ተነሳሽነት፤ብቁና ርህራሄ የተሞላበት የጤና ሰራተኞች በጤና ተቋማት መፍጠር ወሳኝ በመሆኑ የንቅናቀ መድረኩ መዘጋጀቱን ነዉ፡፡ በጤና ተቋማት ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ እና ህብረተሰቡ በሚፈልገዉ መልኩ አገልግሎት እንዲያገኝ ለማድረግ በጤና ተቋማት ተነሳሽነት፤ብቁና ርህራሄ የተሞላበት የጤና ሰራተኞች መፍጠር ለተቋማቱ ስራዎች መሳካት ቁልፍ ተግባር በመሆኑ የጤና ተቋማት ሀላፊዎች እና የሚከለከታቸዉ አካላት ከዚህ ንቅናቄ መድረክ በኋላ በተቋማቸዉ ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸዉ ሀላፊዉ አሰስበዋል፡፡ በንቅናቄ መድረኩ ላይ ከክልል ጤና ቢሮ፤ከአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል፤ከአሶሳ ከተማ ጤና መምሪያ፤ከበ/ጉ/ክ/መ/ትምህርት ቢሮ እና ከአሶሳ ከተማ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ሀላፊዎችና የሚመለከታቸዉ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ የቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል መንግሰት ጤና ቢሮ