Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

አመታዊ የሥራ ግምገማ

በክትባት ለመከላከል በሚቻሉ በሽታዎች ቅኝትና ምላሽ አሰጣጥ ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየተሰራባቸው መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ገለፀ ። ቢሮው ከአለም ጤና ድርጂት ጋር በመተባበር በክትባት ልንከላከላቸው የምንችላቸው በሽታዎች ቅኝት ምላሽ አሰጣጥና መልሶ ማቋቋም ዓመታዊ የስራ ግምገማ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በክልሉ ስራ አመራር ተቋም አካሂደዋል ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ በክትባት ልንከላከላቸው በሚቻሉ በሽታዎች ቅኝት ምላሽ አሰጣጥ ላይ የአለም ጤና ድርጀትን ጨምሮ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በትኩረት እየሰራ ይገኛል ። እነዚህን የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል በባለፉት በ2017 ዓ.ም የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን በመገምገም የተሻሉ ልምድና አሰራሮችን አጠናክሮ ማስቀጠል እና መሻሻል የሚገባቸውን አሰራሮች ላይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ታስቦ የግምገማ መድረኩ መዘጋጀቱን የጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ምላሽ አሰጣጥና መልሶ ማቋቋም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ መብራቱ በጉኖ ገልፀዋል ። የክልል፣የዞን እና የወረዳዎች የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ከቀረበ በሃላ አቶ መብራቱ በጉኖ እንዳሉት በክትባት የምንከላከላቸው በሽታዎች ቅኝት ቁጥጥርና ምላሽ አሰጣጥ ዙርያ በበጀት አመቱ በርካታ አበረታች ስራዎች የተሰሩ መሆኑን በመግለፅ በመረጃ ልውውጥ ፣በናሙና አላላክና ምላሽ አሰጣጥ ላይ ከባለፈው አመት በተሻለ መልክ ተጠናክረው መሰራት እንዳለበት በአፅንኦት ተናገረዋል ። በየደረጃው የሚገኙ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ምላሽ አሰጣጥና መልሶ ማቋቋም ስራዎችን በየመዋቀሮቻቸው የፈጣን ምላሽ አሰጣጥ ግብር ሀይልን በማጠናከር ለሚከሰቱ ወረርሽኞች ፈጣን ምላሽ አሰጣጥ ላይ በልዩ ትኩረት መስራት እንዳለባቸው አቶ መብራቱ በጉኖ ገልጿል ። አቶ መብራቱ አክለውም በክትባት ልንከላከላቸው የምንችላቸው በሽታዎች ቅኝት ፣ ምላሽ አሰጣጥና መልሶ ማቋቋም ስራ ለማጠናከር የአቅም ግንባታ ስራዎችን እና ሌሎችን አሰፈላጊ ሁሉ እገዛ በቢሮ ይደረጋል ብለዋል። በክትባት ልንከላከላቸው የምንችላቸው በበሽታዎችን የቅኝትና ምላሽ አሰጣጥ ስራዎችን የበለጠ ለማጠናከር የግል የጤና ተቋማት እና የመንግስት የጤና ተቋማት መካከል ያለውም ቅንጂታዊ አሰራር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ያሉት ደግም የአለም የጤና ድርጅት የክልሉ ተወካይ አቶ ምትኩ ፊጤ ናቸው ። በመድረኩ ላይ የክልል፣የዞንና የወረዳ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች ተሳትፈዋል ።