Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የ2018 ዕቅድ መፈራረም

በበጀት አመቱ በጤናው ዘርፍ የተያያዙ የጤና ግቦችን ለማሳካት የተናበበና በዉጤት የሚመዘን ዕቅድ መታቀድ እንዳለበት የቤ/ጉ/ክ/መ/ጤና ቢሮ ሀላፊ አሳሰቡ ። የቢሮ ሀላፊዉ ከቢሮ ዳይሬክቶሬቶች ጋር የአመቱን ዕቅድ ተፈራርመዋል ። የቢሮ ሀላፊ አቶ ወልተጂ በጋሎ በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንደአሉት በበጀት አመቱ በጤናው ዘርፍ የተያያዙ የጤና ግቦችን ለማሳካት የተናበበና በዉጤት የሚመዘን ዕቅድ መታቀድ እንደአለበት ነው ። እነዚህ የታቀዱ ዕቅዶች እስከ ፈፃሚ ድረስ በማዉረድ የሚፈለገውን ዉጤት ለማምጣት እያንዳንዱ የሥራ ክፍሎች ሥራዎችን በትኩረት መምራት እንደአለባቸዉ ቢሮ ሀላፊው አሳስበዋል ። የሥራ ክፍሎች በበኩላቸው እንደሀገር የተያዘውን የጤና ግቦች ለማሳካት በበጀት አመቱ የታቀዱ ዕቅዶችን ወደ ዉጤት ለመቀየር በትጋት እንሰራለን ብለዋል። ነሐሴ 19/2017 ዓ.ም