Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የግብር ሀይል ስብሰባ

በተለያዩ ጊዜያት የሚከሰቱ ወረርሽኞችን ለመከላከል የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ ። (27/12/2017 ዓ.ም) በመተከል ዞን ከተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች እና በጤና ላይ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላት ያካተተ ግብረ ሀይል ወደ ሥራ እንዲገባ ተደርጓል ። በመተከል ዞን በተለያዩ ጊዜያት የሚከሰቱ ወረርሽኞችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ዘርፌ ብዙ ተግባራት ሲከናወን እንደነበረ ይታወቃል ። በተከናወኑት ተግባራትም በተለያዩ ጊዜያት የተከሰቱ ወረርሽኞች የከፋ ጉዳት ሳያደርሱ ለመከላከል መቻሉን የመተከል ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ፍቃዱ ደበሎ ገልጸዋል ። ከክረምት ወራት መግባት ጋር ተያይዞ በአንድንድ ወረዳዎች ላይ አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ የኮሌራ በሽታ አዝማሚያዎችን ለመከላከል የዞን ግብረ ሀይሉን ወደ ሥራ ለማስገባት የተዘጋጀ የግብረ ሀይል ስብሰባ መሆኑን ምክትል አሰተዳዳሪዉ ገልፀዋል። አቶ ፍቃዱ አክለውም በዞኑ በአንዳንድ ወረዳዎች አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ የወረርሽኝ ምልክቶች ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሁሉም ሴክተር መ/ቤቶች እና በጤና ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንደአለባቸዉ አሳስበዋል ። የመተከል ዞን ጤና መምሪያ ዶ/ር ታሬቀኝ አርገታ በበኩላቸው ወረርሽኙን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የግብዓት ችገሮች ባይኖርም ግብዓቶችን እስከ ቦታው ለማድረስ ከክረምት ወራት ጋር ተያይዞ የትራንስፖርት ችገሮች እና እስከ ቦታዉ ለማድረስ አስቸጋሪ በመሆኑ የሁሉም አካላት ርብርብ እንደሚጠይቅ ገልጸዋል ። በመድረኩ ላይ የተገኙ አካላት በበኩላቸው በዞኑ በተወሰኑ ወረዳዎች የተከሰተው ወረርሽኝ መሰል በሽታዎች ለመከላከል ከመንግሥት መዋቅሮች ጎን በመቆም የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል ። ግብረ ሀይሉ የክልል፣ የዞንና በጤና ዘርፍ ላይ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተቋቁሟል