Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የህዝብ ግንኘነት መድረክ

በግልገል በለስ ከተማ ለህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች በተለያዩ ወቅታዊ የጤና ጉዳዮች ላይ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ። ወቅታዊ የጤና መረጃዎችን በወቅቱ ለህብረተሰቡ ለማዳረስ እና በተለያዩ ጊዜያት የሚከሰቱ ወረርሽኞችን በጋራ ለመከላከል በወቅታዊ የጤና ጉዳዮች ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ወሳኝ በመሆኑ ስልጠናው መዘጋጀቱ ተገልጿል ። የስልጠናዉ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በወቅታዊ የጤና መረጃዎች ዙሪያ ስልጠና መሰጠቱ በዕውቀት ላይ የተመሠረተ የጤና መረጃ ለመስጠት የጎላ ድርሻ ስለአለው ተጠናክሮ መቀጠል እንደአለበት ጠይቋል ። ነሐሴ 27/2017ዓ.ም