Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

Regional laboratory

በ2017 ዓ.ም በየጤና ተቋማት የሚሰጠዉን የላብራቶሪ አገልግሎት ጥራት ለማስጠበቅ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆናቸው ተገለፀ ። (ነሐሴ 30/2017 ዓ.ም) አመቱ በመተከል ዞን የጤና ተቋማት የተከናወኑ ተግባራት አመታዊ የሥራ ግምገማ በግልገል በለስ ከተማ ተካሂዷል ። በየጤና ተቋማት የሚሰጡ የጤና አገልግሎት ጥራት ማስጠበቅ የሚቻለዉ በጤና ተቋማት የሚሰጡ የላብራቶሪ አገልግሎቶች ጥራት ማስጠበቅ ሲቻል በመሆኑ የክልሉ ላብራቶሪ ማዕከል ከጤና ቢሮና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በክልሉ በሚገኙ የጤና ተቋማት ዘርፈ ብዙ ተግባራት በማከናወን አበረታች ዉጤቶች ማስመዝገብ ተችሏል ። እነዚህ የተጀመሩ ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና በተቋማት መካከል የተሞክሮ ልዉዉጥ ለማድረግ የሥራ አፈጻጸም የግምገማ መድረክ መዘጋጀቱን የክልሉ ላብራቶሪ ማዕከል ዳይሬክተር ወ/ሮ ሶፊያ አወድ ገልጸዋል ። ማዕከሉ የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል በተቋማቱ የተሰሩ የላብራቶሪ ዉጤቶች ትክክለኛነታቸው የማረጋገጥ፣የታችኛውን የጤና ተቋማት የመከታተል እና የዕውቀት ሽግግር ከማድረግ በተጨማሪ ከተለያዩ የባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የአቅም ግንባታ ሥራዎች ሲሰራ መቆየቱን ወ/ሮ ሶፊያ ተናግሯል ። ወ/ሮ ሶፊያ አክለውም እነዚህ የተጀመሩ ሥራዎች ከዳር ለማድረስ ከማዕከሉ መዋቅር ጀምሮ በርካታ ችግሮች በመኖራቸው በሚመለከታቸው አካላት ትኩረት መስጠት እንደአለበት ጠይቀዋል ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል የቢሮ ሀላፊ አቶ አለም ደበሎ በበኩላቸው ክልላዊ የላብራቶሪ ማዕከል በበጀት አመቱ በጤና ተቋማት የሚሰጡ የላብራቶሪ አገልግሎት ጥራት ለማስጠበቅ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች በመሆናቸው ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል። በጤና ተቋማት የሚሰጡ የላብራቶሪ አገልግሎት ጥራት የማስጠበቅ ሥራዎች ከክልላዊ ላብራቶሪ ማዕከል ብቻ የሚጠበቅ ሳይሆን የተቋማት ሀላፊዎችና የወረዳ ጤና ጽ/ቤት ሀላፊዎች ግብዓት ከማሟላት ጀምሮ ሥራውን በትኩረት መከታተል እንደአለባቸዉ አቶ አለም አሳስበዋል ። ለተቋሙ ሥራዎች መሳካት ተግዳሮት ናቸው ተብሎ የቀረቡ ችገሮችን ለመቅረፍ ቢሮው ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመሆን በትኩረት እንደሚሰራ ምክትል የቢሮ ሀላፊዉ ገልጸዋል ። ናሙናን በአግባቡ ወስዶ ለሚመለከተው የጤና ተቋማት የመላክና በወቅቱ በተሰጠው ግብረ መልስ መሠረት የሚደረገው የህሙማን ድጋፍና ክትትል በተፈለገው መልኩ ባለመሆኑ በቀጣይ መስተካከል እንደአለባቸዉ ሀላፊዉ አስገንዝበዋል ። በመድረኩ ላይ በቢሮ፣በክልላዊ ላብራቶሪ ማዕከል፣በሆስፒታሎች እና በጤና ተቋማት በበጀት አመቱ የተከናወኑ ተግባራት የአፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ዉይይት ተደርጎበታል ። ነሐሴ 30/2017 ዓ.ም