Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የበዓል መልዕክት

የቤኒሻንጉል  ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ  እንኳን ለ2018 ዓ.ም  አድሱ አመት   በሠላምና በጤና  አደረሳችሁ  በማለት የመልካም ምኞት መልዕክት  ያስተላልፋል ። ** የቤኒሻንጉል ጉሙዝ  ክልላዊ  መንግስት  ጤና ቢሮ ሀላፊ  አቶ ወልተጅ በጋሎ አዲሱ ዓመት  የአብሮነት፣ የመተሳሰብ፣ የተስፋ  እና የአዲስ ዕይታ የመጀመሪያ ምዕራፍ በመሆኑ እንኳን  አደረሳችሁ  ብለዋል። ዘመን መለወጫ በነበረውና በሚሆነው መካከል ትስስር የሚፈጥርልን ድልድይ በመሆኑ በአዲሱ ዓመት ከምንም በላይ ከመልካም ተሞክሮዎቻችንና ከፈተናዎቻችን ትልቅ ትምህርት በመውሰድ፣ ተስፋን በመሰነቅ ለአዲስ ህይወት ራሳችንን የምናዘጋጅበት ይሆናል፡፡ ያሳለፍነው ዓመት በጤናው ልማት ዘርፍ በርካታ መልካም ውጤቶችን የተመዘገቡበት  በመሆኑ እነዚህ የተመዘገቡ ዉጤቶችን አጠናክረን በማስቀጠል  ጥራት  ያለዉ ቀልጣፋና ፍትህዊ የጤና አገልግሎት  ተደራሽ ለማድረግ  ተግተን  የሚንሰራበት አመት ይሆናል  ብለዋል ቢሮ ሀላፊዉ ። ይህም  እዉን የሚሆነዉ የጤናው ዘርፍ አመራር፣ የጤና ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት  በአዲስ እይታና  ቁጭት  በጋራ በመስራት  በመሆኑ  በበጀት አመቱ ከምንጊዜውም በላይ በአንድነትና በተቀናጀ መልኩ መስራት ከሁላችንም ይጠበቃል ብለዋል። የተከበራችሁ ምስጉን የጤና ባለሙያዎቻችን እና የአስተዳደር ሠራተኞች እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ ደርጅቶችና ባለድርሻ አካላት በ2017 ዓ.ም የክልሉን ህዝብ ከልብ ለማገልገል ላሳያችሁት ተነሳሽነትና በ2017 ዓ/ም በጤናው ሴክተር ለተመዘገበው ስኬት በራሴና በክልሉ መንግስት ጤና ቢሮ  ስም ላቅ ያለ ምስጋና እያቀረብኩ በአዲሱ ዓመት የተሻለ ሥራ ለመስራትና ውጤት ለማስመዝገብ  ርብርብ እንድናደርግ የአደራ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ፡፡ በመጨረሻም አዲሱ ዓመት የጀመርናቸውን ውጥን ሥራዎች ፍሬዎች የምናይበት፣ አዳዲስ የከፍታ ሐሳቦቻችንን ለማሳካት የተግባር ዘሮችን የምንዘራበት፤ በትጋት እና በቁርጠኝነት ለሕዝባችን የገባነውን ቃል የምንፈጽምበት እንዲሆን እመኛለሁ፡፡ አቶ ወልተጅ በጋሎ የቤኒሻንጉል  ጉሙዝ  ክልል ጤና ቢሮ