Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

ድንበር ተሻጋሪ በሽታዎችን ለመከላከል የሁሉም እገዛ ወሳኝ ነው ተባለ

በተለያዩ ጊዜያት የሚከሰቱ ድንበር ተሻጋሪ ወረርሽኞች ለመከላከል የማህበረሰብ ተሳትፎ የጎላ ድርሻ እንደአለዉ ተገለፀ። (07/01/2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ የቀይ መስቀል ማህበር የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅርንጫፍ ከኩርሙ ወረዳ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለተወጣጡ በጎ ፍቃደኞች እና ለጤና ባለሙያዎች በወረርሽኝ መከታተል እና መቆጣጠር ላይ ያተኮረ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል ። የኩርሙክ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አህመድ አዙበር የስልጠና መድረኩን ሲከፊቱ እንደአሉት በተለያዩ ጊዜያት የሚከሰቱ ድንበር ተሻጋሪ ወረርሽኞች ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የማህበረሰብ ተሳትፎ የጎላ ድርሻ እንደአለዉ ነው ። ወረዳዉ በተለያዩ መግቢያዎች ከሌሎች ሀገራት ጋር የሚዋሰን በመሆኑ የስልጠናው መሰጠት በማህበረሰብ እና በሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቅንት ለማጠናከር የጎላ ድርሻ እንደአለዉ የጽ/ቤት ሀላፊው ገልጸዋል ። በማህበረሰብ እና በሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቅንት ማጠናከር መረጃዎችን በወቅቱ ለመሰብሰብ ፣ ወቅታዊ ሪፖርት ለማድረግ ፣ የበሽታ ዳሰሳና ቅኝት በማድረግ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያግዝ መሆኑን አቶ አህመድ ተናግሯል ። በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ምላሽ አሰጣጥ /PREPARE/ባለሙያ ሲስተር ብዙዬ ወዳጄ በበኩላቸው ከተለያዩ ሀገራት ድንበር ተሻግሮ የሚመጡ ድንበር ተሻጋሪ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የጤና ባለሙያዎች እና የበጎ ፍቃደኛ የማህበረሰብ ክፍሎች ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ በመሆኑ የስልጠና መድረኩ መዘጋጀቱን ገልጸዋል ። ስልጠናዉ ከክልል፣ከአሶሳ ዞን፣ከኩርሙክ ወረዳ የተወጣጡ የጤና ባለሙያዎችና ከኩርሙክ ቀበሌ ለተወጣጡ በጎ ፍቃደኛ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል ።