Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የማህበረሰብ መር የኤችአይቪ ጥምረት ምስረታ

ኤች.አይ.ቪ ኤዲስ ስርጭት ለመከላከል የማህበረሰብ መር ክትትል ኳሌሽን ማቋቋም የጎላ ድርሻ እንዳለው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ አስታወቀ ። የመጀመሪያ የሆነዉ የማህበረሰብ መር ክትትል ኳሌሽን ተቋቋመ ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ የኤች.አይ.ቪ ኤዲስ ስርጭትን የመከላከል እና የመቆጣጠር ሥራዎችን ሥራ ዉጤታማ ለማድረግ ዘርፌ ብዙ ሥራዎችን ሲሰራ እንደነበረ ይታወቃል ። እነዚህ የተጀመሩ ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የማህበረሰብ መር ክትትል ኳሌሽን ማቋቋም ማስፈለጉን የቢሮ የዘርፌ ብዙ ኤችአይቪ መከላከል እና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታረቀኝ ወዲ ገልጸዋል ። የዚህ ኳሌሽን መቋቋም ኤች.አይ.ቪ በደማቸው ያለባቸው ወገኖች እና ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በየጤና ተቋማት እያገኙ ያሉት አገልግሎት ተደራሽነት ፣ጥራት እና ከሰብዓዊነት አኳያ እንዲሰጡ ይዳርጋል ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ በጤና ተቋማት የሚሰጠው አገልግሎት ያለበት ሁኔታ መረጃ ለመሰብሰብ፣የሚሰጠዉን አገልገሎት ለመለየት፣መረጃ በመተንተን ለዉሳኔ ሰጪ አካላት ለዉሳኔ በማቅረብ የሚሰዉን አገልግሎት ለማሻሻል እንደሚያግዝ አቶ ታሬቀኝ ገልጸዋል ። የማህበረሰብ መር ክትትል ኳሌሽን/ጥምረት / የሚሰሩ ሥራዎች ዉጤታማነት የጥምረቱ አካላት የበኩላቸውን ድጋፍና ክትትል በፋይናንስም ሆነ በሌሎች ጉዳዮች መደገፍ እንደአለባቸዉ ዳይሬክተሩ ጠይቀዋል ። ይህ የማህበረሰብ መር ክትትል ኳሌሽን/ ጥምረት /በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚቋቋም ሲሆን በክልሉ በተመረጡ የጤና ተቋማት ማለትም አሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል፣ባምባሲ፣አሶሳ ከተማ፣ማምቡክ እና ግልገል በለስ ጤና ጣቢያዎች ላይ ለቀጣይ 6 ወራት የሚቆይ ነው ተብሏል ። የማህበረሰብ መር ክትትል ኳሌሽን/ ጥምረት / የተቋቋመዉ መንግታዊ ከሆኑና መንግታዊ ካልሆኑ ሴክተር መ/ቤቶ የተወጣጣ መሆኑን ከመድረኩ ለመረዳት ተችሏል ።