Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

መረጃ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ በቢሮው በጤናዉ ዘርፍ በዳታ ማናጅመንት ሴንተር የተሰሩ የ2017 ዓ.ም በጀት አመት የስራ አፍጻጸም በክልሉ ስራ አመራር ተቋም ግምገማ አካሂደዋል። ‎ ‎በሪፖርት ግምገማው ላይ በክልሉ ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር እና ምላሽ አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መብራቱ በጉኖ እንዳሉት መረጃ ለጤና ስርዓቱ የጀርባ አጥንትና ለመሪዎችም መረጃ ላይ የተመሰረተ ወሳኔ ለመስጠት አሰፈላጊና አቅጣጫ ጠቋሚ መሆኑን በመግለፅ በክልላችን የተቋቋመው ዳታ ማኔጅመንት ሴንተር በክልሉ የሚገኙትን ማንኛውም የጤናና ጤና ነክ መረጃዎችን ወደ አንድ ማዕከል መሰብሰብ,መተንተን እንዲሁም ለመረጃ ፈላጊዎች በቀላሉ ለማቅረብ ታሳቢ ተደርጎ የተቋቋመ መሆኑን ነዉ። ይህ የመረጃ ማዕከል ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በዳታ አሰባሰብ ፣ መረጃዎችን በመተንተ እና ለዉሳኔ የማቅረብና በአቅም ግንባታ ሥራዎች የተሰሩ ሥራዎች አበረታች በመሆናቸው ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል። ‎የበጀት አመቱን አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት አቶ ደረጀ ሮባ ‎ማዕከሉ በኢትዮጰያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኩል  በኮንትራት በአፈሪካ ሲዲሲ አምስት ሰራተኞች ተቀጥረው እየሰሩ መሆኑን በመግለጽ በክልሉ በመረጃ ላይ እየሰሩ ላሉት ለተለያዩ ሰራተኞች በተለያዩ ሶፈትዌሮች ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ሲሰጥ መቆየቱን ገልፀዋል። በተጨማሪ በክልሉ ላይ የተሰሩ የተለያዮ የሪሰርች መረጃዎችን የተሰበሰቡ መሆኑንና እነዚህን መረጃዎች ለሚፈልገው አካል በቀላሉ እንዲጠቀሙ ለማድርግ የዳታ ሼሪንግ መመሪያ በማዘጋጀት ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራታቸውን አቶ ደረጀ ተናግረዋል ። በመድረኩ ላይ ከሥራ አፈጻጸም ግምገማ በተጨማሪ በመረጃ ጥራት ዙሪያ በክልሉ ባሉት ሶስት ዞኖች  የተሰሩ የዳሰሳ ግኝት ሪፖርት በአቶ መብራቱ ወንደራድ ቀርቦ በቂ ውይይት በማካሄድ የተለዩ ክፈተቶች በ2018 ዓ.ም በጀት አመት የዕቅድ አካል ተደርጎ መሠራት እንዳለባቸው  የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ የሪፖርት ግምገማ መድረክ ግምገማው ተጠናቋል። መስከረም 16/2018 ዓ.ም ‎ ‎ ‎